የእኔ መለያ

ከዴንቨር የህዝብ ቤተ–መጽሐፍት ካርድዎ ምርጡን ለማግኘት እነዚህን ቅንብሮች እና ባህሪያት ይጠቀሙ።

ለመዋስ ያዘዙዋቸው

  • መጽሐፍ ለመዋስ ያዘዙ፦ እራስዎን ወደ ተጠባባቂ ዝርዝር ለማከል የቤተ–መጽሐፍት ካታሎግ ይጠቀሙ። በማንኛውም ጊዜ በ"እኔ መለያ" ውስጥ ለመዋስ ያዘዙዋቸውን መጽሐፍት ማረጋገጥ ይችላሉ
  • መጽሐፉን የሚረከቡበትን ቦታ ይምረጡ ወይም ይቀይሩ፦ መደበኛ የመረከቢያ ቦታዎ አብዛኛውን ጊዜ መጀመሪያ የተመዘገቡበት ቅርንጫፍ ነው፡፡ ያ ቅርንጫፍ ምቹ ካልሆነ - ወይም ለእድሳት ዝግ ከሆነ- የመረጡትን የመረከቢያ ቤተ–መጽሐፍትን በእኔ መለያ የምርጫ ክፍል ውስጥ ማዘመን ይችላሉ። የመረጡት ቦታ ቋሚ መረከቢያዎ እንዲሆን “ሁልጊዜ ይህንን የመረከቢያ ቦታ ተጠቀም” የሚለውን ይምረጡ።
  • እንዴት ማሳወቂያ እንደሚደርስዎት ያዘምኑ፦ ለመዋስ ያዘዙዋቸውን ማሳወቂያዎች ለመቀበል በእኔ መለያ ውስጥ በኢሜል፣ በጽሑፍ ወይም በስልክ ይምረጡ።
  • ከቤት በሚርቁበት ወቅት ለመዋስ ያዘዙዋቸው መጽሐፍ ለጊዜው ያቁሙ፦ በእረፍት ላይ ከሆኑ ለመዋስ ያዘዙዋቸውን መጽሐፍ ለጊዜው ማቆም ይችላሉ ይህም በተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ወደ ላይ መውጣትዎን እንዲቀጥሉ ያደርጋል ነገር ግን በድጋሚ አገልግሎቱን እስኪያነቃቁ ድረስ መጸሐፍቱን እንዲረከቡ አይደረግም።

ለመዋስ ያዘዙዋቸው ገደቦች

ሙሉ መብት ካርድ ያላቸው በአንድ ጊዜ መጠየቅ የሚችሉት ከፍተኛው የመጽሐፍት ብዛት 30 ብቻ ነው። ለጊዜው የታገዱ ጥያቄዎች እንዲሁም ለመረከቢያ የተዘጋጁ እና በጉዞ ላይ ያሉ ጥያቄዎች በ30 መጽሐፍት ጥያቄ ገደብ ውስጥ አይካተቱም።

Prospector (የፕሮስፔክተር)

የ30 የጥያቄ ገደባቸው የደረሱ ደንበኞች የፕሮስፔክተር ጥያቄዎችን ከማስቀመጥ ይከለከላሉ።

WorldCat (ወርልድካት)

እያንዳንዱ ደንበኛ በማንኛውም ጊዜ በድምሩ 10 በወርልድካት ጥያቄዎች ብቻ የተገደበ ነው። የዎርልድካት ጥያቄዎች በILLiad ራሱን የቻለ ሪኩዌስት ኢት ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግበት ሲሆን መጻሕፍቱ በዴንቨር የሕዝብ ቤተ–መጽሐፍት እጅ እስኪገቡ ድረስ በዴንቨር የሕዝብ ቤተ–መጽሐፍት መለያዎ ውስጥ አይታዩም።

ማሳሰቢያ፦ ጊዜያዊ የካርድ ባለቤቶች እስከ 10 የሚደርሱ የዴንቨር የሕዝብ ቤተ–መጽሐፍት እቃዎችን ሊጠይቁ ይችላሉ ነገር ግን ለፕሮስፔክተር እና ለወርልድካት ብቁ አይደሉም።

ለመረከቢያ የተዘጋጁ ደረጃ ላይ ያሉ መጻሕፍት ለርሶ ዝግጁ ናቸው፤ እነዚህም በመረከቢያ መደርደሪያው ላይ በድምሩ ለ7 ቀናት ይቆያሉ።

ለተወሰኑ ቁሳቁሶች የተፈቀዱትን የውሰት እና የማደሻ ጊዜያት ይመልከቱ።

ማሳወቂያዎች

የመመለሻ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ለመረከቢያ ዝግጁ የሆኑ ጥያቄዎችን በተመለከተ መረጃ እንዲደርስዎ በየእኔ መለያ ውስጥ የማሳወቂያ ምርጫዎን ያዋቅሩ፡፡ በኢሜይል ወይም በጽሁፍ መልእክት መረጃ እንዲደርሳቸው ያደረጉ ደንበኞች፣ መጽሐፉ መመለስ ካለበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ የቅድመ ማሳሰቢያ ወይም የራስ-ሰር ማደሻ መረጃ ይላክላቸዋል፡፡

የጽሑፍ ማሳወቂያ ይገኛል

ለመዋስ ያዘዙዋቸውን እና የመመለሻ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ቁሳቁሶች በተመለከተ በጽሁፍ መልእክት የማሳወቅ አገልግሎት ዳግም ስራ ጀምሯል። የጽሑፍ ማሳወቂያዎችን ለማንቃት (ወይም እንደገና ለማንቃት)፣ የማሳወቂያ ምርጫዎችዎን ለማዘመን ወደ የእኔ መለያ ይግቡ እና ወደ የእውቂያ መረጃ እና ምርጫዎች ይሂዱ።

የመመለሻ ቀናቸው ለቀረቡ ቁሳቁሶች የሚላኩ የቅድመ ማሳሰቢያዎች እና የራስ-ሰር ማደሻ አገልግሎቶች

የእኛ ሥርዓት ለዕድሳት ብቁ የሆኑ በውሰት የተወሰዱ ቁሳቁሶችን የመመለሻ ቀናቸው አንድ ቀን ሲቀረው በራስ-ሰር ለማደስ ይሞክራል፡፡ በራስ-ሰር ስለታደሱ እና መመለሻቸው ስለቀረበ ቁሳቁሶች የቅድመ ማሳወቂያዎች እንዲደርስዎ የኢሜይል ወይም የጽሁፍ መልእክት ማሳወቂያን ይምረጡ፡፡ ሊታደሱ የማይችሉ ቁሳቁሶች መመለሻቸው ባለፈ በ7ኛው፣ በ14ኛው እና በ21ኛው ቀን የዘግይቶ መመለሻ ማሳሰቢያዎች ይላካሉ። ሁለቱም የእንግሊዝኛ እና የስፓኒሽ የማሳወቂያ አማራጮች ይገኛሉ።

ለተቀመጡ ፍለጋዎች የኢሜይል ማሳወቂያዎች

ለሚደጋገሙ ፍለጋዎችዎ የኢሜይል ማሳወቂያዎችን ያግኙ፡፡ የሚፈልጉትን ለማግኘት ካታሎጉን ይፈልጉ እና “ፍለጋን አስቀምጥ” ላይ ጠቅ ያድርጉ። ለፍለጋው ስም ይስጡት፣ በየሳምንቱ ወይም በየወሩ ለማሄድ ይምረጡ እና ቤተ–መጽሐፍቱ ከፍለጋዎ ጋር የሚዛመዱ አዳዲስ እቃዎችን ወደ ስብስባችን ሲያክል ኢሜይል ይደርስዎታል።

የንባብ ታሪክ

የንባብ ታሪክዎን መዝግቦ ለመያዝ ፍቃድ ይስጡ። እቃዎቹ ሲመለሱ በንባብ ታሪክዎ ላይ ይታያሉ። ታሪክዎን በርዕስ፣ በደራሲ፣ በሚዋስበት ቀን፣ ቅርጸት ወይም በአበዳሪ ቤተ-መጽሐፍት ይመልከቱ። ማቆየት የማይፈልጓቸውን የግል ርዕሶች ይሰርዙ። የንባብ ታሪክዎን በማንኛውም ጊዜ ማቋረጥ ይችላሉ፤ አገልግሎቱን ሲያቋርጡም ሁሉም የተቀመጡ መዝገቦች ወዲያውኑ ይሰረዛሉ።

ዝርዝሮችን ማተም፣ ኢሜይል መላክ እና ማስቀመጥ

ከፍለጋ ውጤቶችዎ ውስጥ የመጽሐፍት ርዕሶችን ያክሉ፤ እንዲሁም ዝርዝሮችን በኢሜይል ይላኩ፣ ያትሙ ወይም ያስቀምጡ፡፡ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውል ዝርዝር ዎርኪንግ ሊስት ለማዘጋጀት ወደ ዝርዝሬ አክል የሚለውን ጠቅ ያድርጉ፤ ዝርዝርዎ ተቀምጦ በኋላ ላይ መልሰው ለማግኘት ግን ወደ የእኔ መለያ ይግቡ፡፡ ርዕሶችን በመሰረዝ ወይም እቃዎችን ከአንድ ዝርዝር ወደ ሌላ በማዛወር ዝርዝሮችዎን ያስተዳድሩ። ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ለመጽሐፍት ዝርዝሮችን ለዋቢ መጻሕፍት አዘገጃጀት በሚመች መልኩ ማስተካከል ይችላሉ።

የመጽሐፍ መለያ ቁጥርን በጽሁፍ መልእክት መላክ

እርሳስ እና ወረቀት መጠቀም አያስፈልግዎትም፤ ለአንድ ቁሳቁስ የተሰጠውን መገኛው የሚገልጽ መረጃ አጠገብ የሚገኘውን የሞባይል ስልክ ምልክት ( ) በመጫን የመጽሐፍ መለያ ቁጥሩን ለራስዎ ወይም ለጓደኛዎ በጽሁፍ መልእክት መላክ ይችላሉ።

በDPL ባለቤትነት ያልተያዙ እቃዎችን መጠየቅ

የሚፈልጉትን ቁሳቁስ በእኛ የኢንተርኔት ካታሎግ ውስጥ ማግኘት ካልቻሉ፣ ከሌላ የቤተ–መጽሐፍት ሥርዓት እንዲመጣልዎ መጠየቅ ይችላሉ፤ ወይም ቤተ–መጽሐፍቱ መጽሐፉን ለመግዛት ሊወስን ይችላል፡፡

የባህል አጋሮች

ማይ ዴንቨር ካርድ ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 18 ለሆኑ የዴንቨር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዴንቨር የመዝናኛ ማዕከላት በነፃ እንዲገቡ የሚያስችል ሲሆን፣ እንደ ቤተ–መጽሐፍት ካርድም ሊያገለግል ይችላል፡፡