ተንቀሳቃሽ የቤተ–መጽሐፍት አገልግሎቶች

የቤተ–መጽሐፍት አገልግሎት መዳረሻ እንቅፋቶችን ለማፍረስ ቁርጠኞች ነን። የመጽሐፍት ተንቀሳቃሽ መኪናዎቻችን በዴንቨር ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የመኖሪያ አካባቢዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና የማህበረሰብ ቦታዎችን በመዘዋወር የቤተ–መጽሐፍት ግብዓቶችን በቀጥታ ተደራሽ ያደርጋሉ፡፡ በተጨማሪም፣ ማህበረሰባችን ቤተ–መጽሐፍቱ ከሚያቀርባቸው  እድሎች ጋር እንዲገናኝ ለማድረግ፣ በአካባቢው በሚከናወኑ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት የቤተ–መጽሐፍት አገልግሎቶችን በንቃት እናስተዋውቃለን።

አገልግሎቶችን መጠየቅ

የተንቀሳቃሽ አገልግሎቶች የሚገኙት በዴንቨር ከተማ እና ካውንቲ ውስጥ ብቻ ነው። ሁሉም የአገልግሎት ጥያቄዎች የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። የመጽሐፍት ተንቀሳቃሽ መኪናዎች እና የማዳረሻ አገልግሎቶች በአየር ሁኔታ መመሪያዎቻችን መሰረት ሊዘገዩ ወይም ሊሰረዙ ይችላሉ።