ዓላማ
የዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ("ቤተ-መጽሐፍት") ከ18 አመት በታች ለሆኑ ቤተሰቦች እና ግለሰቦች ደህንነቱ የተጠበቀ እና እንግዳ ተቀባይ አካባቢ ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው ("ላልደረሱ ልጆች")። የቤተ-መጽሐፍት መገልገያዎችን አስደሳች ቦታ ለማድረግ እና የመጽሀፍትን፣ የማንበብ እና የመማር ፍቅርን ለማበረታታት፣ ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆች የተሰየሙ ቦታዎችን፣ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን እናቀርባለን። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችዎን ቤተ-መጽሐፍትን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ እና መጽሀፎችን እና ቁሳቁሶችን በመምረጥ፣ ኮምፒውተሮችን በመጠቀም ወይም ፕሮግራሞችን በመከታተል እንደሚረዱዋቸው ተስፋ እናደርጋለን። በጋራ፣ የዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍትን ስንጎበኝ አስደሳች እና አዎንታዊ ተሞክሮ ማቅረብ እንችላለን።
ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች አካባቢዎችን መድረስ
በተለየ ሁኔታ የወጣት ደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጁ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የተነደፉ ቦታዎች አሉ። በእነዚህ አካባቢዎች የሚቀመጡ ጎልማሶችን ለታለመለት አላማ የማይጠቀሙ ከሆነ ወደሌሎች የቤተ-መጽሐፍት ቦታዎች እንዲዛወሩ ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ቤተ-መጽሐፍቱን ለቀው እንዲወጡ በቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ይጠይቃሉ። የሰራተኞች አባላት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ደህንነት በቅድሚያ በቤተ-መጽሐፍቱ ውስጥ ያስቀምጣሉ። ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆች እንክብካቤ እና ኃላፊነት ያለባቸው አዋቂዎች እነዚህን የተመደቡ ቦታዎችን እና በእነዚያ አካባቢዎች የሚገኙትን መጸዳጃ ቤቶች እንዲጠቀሙ የሚፈቀድላቸው ብቸና አዋቂዎች ናቸው።
ከወላጅ/አሳዳጊ የሚጠበቁ ነገሮች እና ኃላፊነቶች
ቤተ-መጽሐፍቱ የህዝብ ቦታ እንደመሆኑ መጠን ለአካለ መጠን ላልደረሰ ልጅ ደህንነትን ሊረጋገጥ አይችልም። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች እንደ ደረጃዎች፣ አሳንሰሮች፣ በሮች፣ የቤት እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ወይም ከሌሎች የቤተ-መጽሐፍት ደንበኞች ጋር ያሉ ግንኙነቶችን የመሳሰሉ አደጋዎች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። በቤተ-መጽሐፍት ግቢ ውስጥ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ስነ–ባህሪ፣ ደህንነት እና ክትትል የወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና ተንከባካቢዎች የአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን የመቆጣጠር ሃላፊነት አለባቸው። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆቻቸውን የክትትል ፍላጎቶችን የመወሰን እና ይህንኑ ክትትል የመስጠት ኃላፊነት የወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና የተንከባካቢዎች ነው። የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች የቤተ-መጽሐፍት መገልገያዎችን ለሚጎበኙ ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆች ደህንነት እና ለጤናቸው ዋጋ ቢሰጡም ታዳጊዎቹ የቤተ-መጽሐፍት መገልገያዎችን በሚጎበኙበት ጊዜ የእንሱ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና ተንከባካቢዎች ብቻ ተገቢውን ክትትል ሊያደርጉ ይችላሉ። ቤተ-መጽሐፍቱም ሆኑ ሰራተኞቹ በ"loco parentis" (በወላጆች ምትክ) ሆነው አይሰሩም። በወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና ተንከባካቢዎች የሚሰጠው ተገቢውን ክትትል የቤተ-መጽሐፍት ሰራተኞች በሁሉም እድሜ ላሉ የቤተ-መጽሐፍት ደንበኞች አስደሳች እና ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ እንዲፈጥሩ ያግዛቸዋል።
የሰራተኞች ሚና
የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ብዙ ግዴታዎች አሏቸው እና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን በቤተ-መጽሐፍት ውስጥ ወይም አካለመጠን ያላደረሱ ልጆች ከህንጻው ሲወጡ መቆጣጠር አይችሉም። ነገር ግን፣ የቤተ-መጽሐፍቱ ባልደረባ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ አግባብ ያለው የወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ ቁጥጥር ከሌለው በቤተ-መጽሐፍት ግቢ ውስጥ ለመገኘት በቂ ብቃት እና ብስለት ላይኖረው ይችላል የሚል ስጋት ካደረባቸው፣ የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኛ ሁኔታውን ለማስተካከል እርምጃ ሊወስድ እና ስጋቶቹን እና የተወሰዱትን እርምጃዎች ለቤተ-መጽሐፍቱ አስተዳደር ያሳውቃል።
ለሁሉም ሰው አወንታዊ የቤተ-መጽሐፍት ልምድን ለማረጋገጥ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ያለ ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ ቁጥጥር በቤተ-መጽሐፍት ግቢ ውስጥ ለመገኘት በቂ ብቃት ወይም ብስለት የሌለው መስሎ ከታየው የሚከተለውን ያደርጋል፡-
- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ከታመሙ፣ ከተራቡ ወይም ከተበሳጩ የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች እነሱን ለማጽናናት ይሞክራሉ። የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ በቤተ-መጽሐፍት ውስጥ ለማግኘት እና ለአካለ መጠን ላልደረሰው ልጅ ደህንነት የቤተ-መጽሐፍቱ ያለውን ስጋት ለመግለጽ እና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የቤተ-መጽሐፍቱን የደህንነት ፖሊሲ ለማቅረብ የተቀናጀ ጥረት ያደርጋሉ። የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ወላጅን፣ አሳዳጊውን ወይም ተንከባካቢውን በቤተ-መጽሐፍት ውስጥ ማግኘት ካልቻሉ፣ የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች አካለመጠን ያልደረሰውን ልጅ እንዲወስዱት ወላጅን፣ አሳዳጊን ወይም ተንከባካቢን ለማግኘት የተቀናጀ ጥረት ያደርጋ። የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆች ደህንነት ያለውን የቤተ-መጽሐፍት ስጋት ይገልፃሉ እና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የቤተ-መጽሐፍት የደህንነት ፖሊሲን ያብራራሉ። ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢው በተመጣጣኝ ጊዜ ውስጥ ሊገኙ ካልቻሉ፣ የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ለአካለ መጠን ያልደረሰውን ልጅ ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ ለማግኘት ወደ ዴንቨር ፖሊስ ዲፓርትመንት ይደውላሉ። የዴንቨር ፖሊስ ዲፓርትመንት ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ኃላፊነት ይወስዳል። እንደዚህ አይነት ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ በማንኛውም ምክንያት ለሚፈጠረው የሲቪል ወይም የወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ይችላል። የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች የዴንቨር ፖሊስ ዲፓርትመንት ስለ ሁኔታው እንደተገለጸለት ለቤተ-መጽሐፍት ደህንነት ቡድን ያሳውቃሉ።
- የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ሠራተኞች ማንኛውም ያለአሳዳጊ የመጣ ሕፃን የቤተ-መጽሐፍቱ ቅርንጫፍ መዝጊያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ወላጆቹን፣ አሳዳጊውን ወይም ተንከባካቢውን እንዲያገኝ ያበረታታሉ። ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ መድረስ ካልቻሉ፣ ወይም ቤተ–መጽሐፍቱ ከተዘጋ በኋላ በ15 ደቂቃ ውስጥ መድረስ ካልቻሉ፣ የቤተ–መጽሐፍቱ ሰራተኞች ለደህንነት ሲባል ለአካለ መጠን ያልደረሰውን ልጅ ለመውሰድ ለዴንቨር ፖሊስ መምሪያ ይደውላሉ። የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ስለ ሁኔታው ለዴንቨር ፖሊስ እንዳሳወቁ ለቤተ-መጽሐፍት ደህንነት ቡድን ያሳውቃሉ። የቤተ-መጽሐፍት ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ለአደጋ ጊዜ ሲዘጋ እነዚሁን እርምጃዎች ይከተላሉ። ወላጅ፣ አሳዳጊ፣ ተንከባካቢ ወይም ፖሊስ እስኪመጣ ድረስ ቢያንስ ሁለት የቤተ-መጽሐፍት ሰራተኞች ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ጋር ይቆያሉ። አንዴ ለአካለ መጠን ያልደረሰው ልጅ በዴንቨር ፖሊስ ዲፓርትመንት ጥበቃ ውስጥ ከሆነ፣ ማሳሰቢያ ከቤተ-መጽሐፍቱ መግቢያ ወይም መግቢያዎች ጋር ከሚከተለው መረጃ ጋር ይያያዛል፦ “ያለ አሳዳጊ የመጡ ልጆች በዴንቨር ፖሊስ ክትትል ስር እንዲቆዩ ይደረጋሉ።” ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅም ሆነ የወላጅ፣ የአሳዳጊ ወይም የተንከባካቢ ስም በማሳሰቢያው ላይ አይዘረዘርም። እንደዚህ አይነት ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ በማንኛውም ምክንያት ለሚፈጠረው የሲቪል ወይም የወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ይችላል።
- የቤተ-መጽሐፍቱ ሰራተኞች ምንም አይነት ክትትል ያልተደረገላቸው ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ከቤተ-መጽሐፍት፣ በአካለ መጠን ባልደረሰው ልጅ ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ በተገለጹ ማንኛውንም ቦታን ጨምሮ ወደ ሌላ ቦታ አያጓጉዙም፡፡
ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የደህንነት ፖሊሲን መተግበር
ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የደህንነት ፖሊሲን ማክበር ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ይከናወናል፡፡ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና ተንከባካቢዎች ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን በቤተ-መጽሐፍቱ ውስጥ ያለ ክትትል የመተው አደጋን ይገነዘባሉ እና ቤተ-መጽሐፍቱን ሊነሱ ከሚችሉት ወይም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጃቸውን ወክለው ሊነሱ ከሚችሉት የይገባኛል ጥያቄዎች ሁሉ ነጻ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የደህንነት መመሪያ በዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ኮሚሽን ከተቀበሉት ሁሉም ፖሊሲዎች እና ሂደቶች ጋር በማጣመር መነበብ አለበት፤ እንደዚህ ያሉ ፖሊሲዎች ያለገደብ https://www.denverlibrary.org/content/library-policies-resources ላይ የሚገኘውን የቤተ-መጽሐፍት አጠቃቀም ፖሊሲን ሊያካትቱ ይችላሉ። ይህ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የደህንነት መመሪያ በዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ኮሚሽን በራሱ ፍቃድ ሊሻሻል ወይም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊደገም ይችላል፡፡
ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የደህንነት ፖሊሲ በዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ለኮሚሽኑ ግምገማ ፌብርዋሪ 2025 ተሻሽሏል።