በዴንቨር ውስጥ ነፃ እና ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው የቴክኖሎጂ ግብዓቶች

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው ማርች 18፣ 2024

ይህ የነፃ እና የዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ዝርዝር የተዘጋጀው በዴንቨር ዲጂታል ኢኩዊቲ ኮኦሊሽን* ነው።

ነጻ የኮምፒዩተር እና የኢንተርኔት አገልግሎት በቤተ-መጽሐፍት

በቤተ-መጽሐፍት ውስጥ ይገናኙ

ሁሉም ክፍት የሆኑ ቅርንጫፍ ቤተ-መጽሐፍቶች ከነፃ የዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ካርድ ጋር ለመጠቀም በውስጡ የሚገኙ የህዝብ ኮምፒውተሮች አሏቸው። ከዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ሕንፃዎችን ውጭ 24/7 ነፃ የዋይፋይ አገልግሎት ይገኛል።

በቤት ውስጥ ይገናኙ

አሁን ከዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት (DPL) ክሮምቡኮችን እና የኢንተርኔት ሆትስፖቶችን ለ21 ቀናት በቤት ውስጥ ለመጠቀም መበደር ይችላሉ። የዴንቨር ነዋሪዎች፣ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ቋሚ የDPL ቤተ-መጽሐፍት ካርድ ያላቸው ነዋሪዎች እነዚህን እቃዎች በሙሉ መብት በነፃ መበደር ይችላሉ። ለክሮምቡክ፣ ለገመድ አልባ መገናኛ ነጥብ ወይም ሁለቱንም አንድ ላይ በቤተ–መጽሐፍቱ የመስመር ላይ ካታሎግ በኩል ወይም በ720-865-1111 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ። በማንኛውም ክፍት ቤተ–መጽሐፍት ቦታ በአካል በመሄድ ወይም በመኪና ማቆሚያ በኩል ወደ ወስጥ መግባት ሳይጠበቅብዎት መውሰድ ይችላሉ፤ እንዲሁም መመለሻው በሁሉም የDPL ቦታዎች ይገኛል።

ዝቅተኛ ዋጋ ያለው የቤት ኢንተርኔት

PCs for People (PCs ፎር ፒፕል) የሞባይል ኢንተርኔት ሆትስፖቶች

PCs for People ያልተገደበ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤልቲኢ የኢንተርኔት አገልግሎት፣ የሞባይል ሆትስፖት፣ ያለ ክሬዲት ቼክ ወይም የተደበቁ ክፍያዎች የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ይሰጣል። ሞደም መግዛት ያስፈልጋል እና የወርሃዊ አገልግሎት $15/በወር ነው። በመስመር ላይ ይዘዙ፣ በ720-278-7725 ይደውሉ ወይም ወደ ኖርዝዌስት ፓርክ ሂል ኮሚኒቲ ቴክኖሎጂ ማዕከል፣ 6035 E. 38th Ave፣ ዴንቨር፣ 80207 በማንኛውም ጊዜ ከሰኞ-አርብ ከ10-5:30 pm ይሂዱ።

ኮምካስት ኢንተርኔት ኤሴንሻልስ

ብቁ ለሆኑ ተመጣጣኝ፣ ቅናሽ የተደረገበት የቤት ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት። ሁለት ደረጃዎች አሉ፦ ኢንተርኔት ኤሴንሻልስ ($9.95/ወር፣ 50 Mbps) ወይም ኢንተርኔት ኤሴንሻልስ ፕላስ ($29.95/ወር፣ እስከ 100 Mbps)። በመስመር ላይ ያመልክቱ ወይም በ (855) 846-8376 ይደውሉ።

ነፃ የህዝብ ገመድ አልባ ኢንተርኔት (ዋይፋይ)

አገልግሎት ለማግኘት የዋይፋይ ኢንተርኔት ይክፈቱ፣ የዋይፋይ አገልግሎት ከሚሰጥበት ስፍራ ቢያንስ በ100-300 ጫማ ርቀት ውስጥ መሆን ይኖርብዎታል። በአገልግሎት ክልል ውስጥ ሲሆኑ፣ ከዋይፋይ ዝርዝር ውስጥ የአገልግሎት ሰጪውን ስም ይመለከታሉ ከዚያም ከዋይፋዩ ጋር ማገናኘት ይቻላል።

  • በዴንቨር የህዝብ ቤተ-መጽሃፍት መኪና ማቆያ ስፍራዎች የቤተ-መጽሃፍት አገልግሎት አቅራቢያ ይገኛሉ። ኔትወርክ፦ DPLWireless
  • በዴንቨር የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ከDPS ትምህርት ቤቶች ወይም መኪና ማቆሚያ ስፍራዎች አቅራቢያ ይገኛሉ። ኔትወርክ፦ DPS Guest
  • በዴንቨር ከተማ በከተማው ህንጻዎች እና መኪና ማቆሚያ ስፍራ ይገኛል። ኔትወርክ፦ DenverGuest Wifi
  • XFinity Lift Zones (የኤክስፊኒቲ ሊፍት ዞንስ) እንደ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና የማህበረሰብ ማዕከላት ባሉ ደህንነታቸው በተጠበቁ ቦታዎች ላይ ነፃ የዋይፋይ መዳረሻ ይሰጣሉ። መዳረሻው እንደ አካባቢ ሰዓቶች እና ፖሊሲዎች ይለያያል።
  • አከባቢያዊ የንግድ ተቋማት፦ እንደ ማክዶናልድስ እና ስታርባክስ ያሉ አንዳንድ የንግድ ተቋማት በመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች የዋይፋይ አገልግሎት ሊሰጡ ይችላሉ። የዋይፋይ ኔትዎርክ ስሞች እና የሚያስጠቅሙበት ሁኔታ ይለያያል።

የሞባይል ስልክ ቴዘሪንግ

አንዳንድ የግል ሞባይል ስልኮች ሌሎች ስልኮችን የኢንተርኔት አገልግሎት ሊያስጠቅሙ ይችላሉ ይህ ማለት የሞባይል ስልክዎን ውሂብ/ኢንተርኔት በመጠቀም፣ ሌሎች መሳሪያዎች ከኢንተርኔት ጋር ኢንዲገናኙ ማድረግ ይችላሉ። ተጨማሪ ክፍያዎች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ስለዚህ ለተጨማሪ መረጃ የአገልግሎት አቅራቢዎን ያነጋግሩ።

ኮምፒውተሮች እና መሳሪያዎች

PCs for People (PCs ፎር ፒፕል)

PCs for People የተለያዩ በጣም ከፍተኛ ቅናሽ ያላቸውን፣ ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን መሳሪያዎች (ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ላፕቶፖች፣ መለዋወጫዎች፣ ገመድ አልባ ሆትስፖቶች) ብቁ ለሆኑ ሰዎች ያቀርባል፣ በአጠቃላይ ከ$10 እስከ $150 ዶላር ዋጋ አላቸው። በመስመር ላይ ማዘዝ ይችላሉ ወይም ዴንቨር ከሚገኝ ማከማቻ መቀበል ይችላሉ። ኮምፒውተሮች የ1 ዓመት ዋስትና እና የደንበኛ ድጋፍ ጋር ይመጣሉ። በአነስተኛ ዋጋ የኮምፒዩተር ጥገናም ያከናውናሉ። ስልክ፦ 720-278-7725

ኮምካስት ኢንተርኔት ኤሴንሻልስ

የኮምካስት ኢንተርኔት ኤሴንሻልስ ደንበኛ ከሆኑ፣ ክሮምቡክ ወይም የዊንዶውስ ላፕቶፕ በ$149.99 ለመግዛት በራስ-ሰር ብቁ ይሆናሉ። በመስመር ላይ መግዛት ይችላሉ።

ህትመት፣ ማባዛት፣ ስካን እና ፋክስ

የዴንቨር የሕዝብ ቤተ–መጽሐፍት

ህትመት፣ ማባዛት፣ ፋክስ መላክ እና ስካን ማድረግ በሁሉም የዴንቨር ህዝብ ቤተ–መጽሐፍት ይገኛል። ህትመት እና ማባዛት በአንድ ደንበኛ በቀን 100 ገጾች ብቻ የተገደበ ነው።

የሚከፈልባቸው አገልግሎቶች

የህትመት፣ የማባዛት፣ የስካን እና የፋክስ አገልግሎቶች Staples (ስቴፕልስ)፣ Kinkos/FedEx (ኪንኮስ/ፌድኤክስ) እና Office Depot (ኦፊስ ዴፖት) አካባቢዎች ይገኛሉ፤ እንዲሁም በአብዛኛዎቹ King Soopers (የኪንግ ሱፐርስ) አካባቢዎች ፋክስ ማድረግ ይቻላል።

የቴክኖሎጂ እገዛ እና ድጋፍ ያግኙ

የዴንቨር የሕዝብ ቤተ–መጽሐፍት

DPL በአካልም ሆነ በምናባዊ የቴክኖሎጂ እገዛን ይሰጣል፡

  • ዲጂታል ናቪጌተሮች የራስዎን ላፕቶፕ ወይም ሌላ መሳሪያ ለማግኘት፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኢንተርኔት ለማግኘት እና ቴክኖሎጂን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ለመማር ነፃ እና ቀጣይነት ያለው እገዛ ያቀርባሉ። ከዲጂታል ናቭጌተር ጋር ቀጠሮ ለማስያዝ በ720-865-3446 ወይም 720-865-1111 ይደውሉ ወይም ኢሜል ወደ dignav@denverlibrary.org ይላኩ!
  • በ720-865-1111 በመደወል ከማህበረሰብ ቴክኖሎጂ ማዕከል ሰው ጋር የአንድ ለአንድ የቴክኖሎጂ እገዛ ቀጠሮ መጠየቅ ይችላሉ።
  • ሁሉም የዴንቨር ህዝብ ቤተ–መጽሐፍት ቦታዎች የህዝብ ኮምፒውተሮችን ለሚጠቀሙ ደንበኞችን እገዛ ይሰጣሉ።
  • የድሮፕ ኢን ቴክ እገዛ በከተማው ውስጥ በሚከተሉት ቦታዎች ይገኛል፦
    • በየሁለት ሰኞ፡ ከ3 ሰዓት - 4፡30 p.m. - የሞንትቤሎ ቅርንጫፍ ቤተ–መጽሐፍት
    • እሮብ፣ ከ11:30 - 1:30 p.m.- የሳም ጋሪ ቅርንጫፍ ቤተ-መጽሐፍት
    • እሮብ፣ ከ2 - 4 p.m. - የሮዶልፎ “ኮርኪ” ጎንዛሌስ ቅርንጫፍ ቤተ-መጽሐፍት
  • ከቤተ-መጽሐፍት ባለሙያ ጋር ይወያዩ
  • ለቤተ-መጽሐፍትት ባለሙያዎች ኢሜይል ይላኩ
  • ለቤተ-መጽሐፍት ባለሙያ በ720-865-1111 ይደውሉ
  • እራስዎን ያስተምሩ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች

Senior Planet (ሲኒየር ፕላኔት ዕድሜያቸው 60+ ብቻ)

ሲኒየር ፕላኔት ከ60 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች የአካባቢ እና ብሔራዊ የቴክኖሎጂ እገዛ በስልክ መስመር ያቀርባል። ከሰኞ እስከ አርብ ከ9:30am እስከ 5:00pm ባለው ጊዜ ውስጥ፣ ለዴንቨር ሲኒየር ፕላኔት ማዕከል በ720-328-0875 መደወል ወይም ከሰኞ እስከ አርብ ከ7am እስከ 6pm ባለው ጊዜ ውስጥ ከሆነ ሰው ጋር ወዲያውኑ ለመነጋገር በ888-713-3495 ብሔራዊ የስልክ መስመር መደወል ይችላሉ። ሲኒየር ፕላኔት ሰዎች በመስመር ላይ መገኘት እንዲችሉ እና ከሌሎች ጋር መገናኘት እንዲችሉ የሚያግዙ በርካታ መመሪያዎችን እና ቪዲዮዎችን አሳትሟል።

ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው የኢንተርኔት እና የኮምፒውተር ቅናሾች

EveryoneOn Offer Locator (ኤቭሪዋንኦን ኦፈር ሎኬተር)፣ ኤቭሪዋንኦን ናሽናል ሎኬተር የሚለውን በመጠቀም በአከባቢዎ የሚገኙ አነስተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች እና ኮምፒዩር ሻጮችን ይፈልጋል። ዚፕ ኮድዎን አስገብተው ጥቂት ጥያቄዎችን በመመለስ እርስዎ ሊያገኙት የሚችሉት ቅናሽ ምን እንደሆነ ይለዩ።

 

ይህ የሀብት ዝርዝር የተዘጋጀው በዴንቨር ዲጂታል ኢኩዊቲ ኮኦሊሽን ሲሆን ከተለያዩ የከተማ ኤጀንሲዎች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የተውጣጡ ተወካዮችን ጨምሮ የአካባቢ ባለድርሻ አካላት ቡድን በዴንቨር ከተማ ውስጥ ያለውን ዲጂታል ልዩነት ለመፍታት እና ዲጂታል ኢኩዊቲ ለማሻሻል በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

በዴንቨር ውስጥ ነፃ እና ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው የቴክኖሎጂ ሀብቶች በእንግሊዝኛ ወይም በስፓኒሽ ሊታተሙ የሚችሉ PDF

Written by angela on