የዌቡ ርዕስ፡ የዴንቨር የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት የእስያና የፓሲፊክ ደሴቶች ማህበረሰብ አባሎቻችን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን ጥቃት ያወግዛል፡፡

ውድ የቤተ-መጻሕፍታችን ማህበረሰቦች፤

የዴንቨር የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት በመላው ሃገር በየጊዜው እየጨመረ የሚገኘውንና በእስያና የፓሲፊክ ደሴቶች ማህበረሰብ አባሎቻችን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን ጥቃት በጽኑ ያወግዛል፡፡ በእስያና የፓሲፊክ ደሴቶች ማህበረሰብ አባሎቻችን፤ ማህበረሰባችሁ እየገጠመው የሚገኘውን ጥላቻና ጥቃት የምንረዳ ሲሆን ከጎናችሁ የምንቆም መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ከዚህ እንደገና ከተፈጸመ አሰቃቂ ድርጊት ማግስት ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች፣ ከተጎጂ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሃዘናቸውን እንጋራለን፡፡

በዚህ ሣምንት በጆርጂያ የተፈጸሙት ድርጊቶች ባለፈው ዓመት ውስጥ የእስያና የፓሲፊክ ደሴቶች ማህበረሰቦች ያለፉበት ተከታታይነት ያለው የጥቃት ድርጊት አካል ነው፡፡ ድርጊቶቹ እነዚህ ማህበረሰቦች እዚህ በዴንቨር ውስጥ የነበረንን ታሪክ ጨምሮ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ በማናቸውም ደረጃዎች ችለው ያሳለፉትን ጥቃት የሚያንጸባርቁ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የዚህ ሣምንት ሁኔታዎች የጥላቻ ወንጀል ተደርገው ያልተመደቡ ቢሆንም እዚህ ደረጃ እንድንደርስ ያደረጉንን መሠረታዊ የዘረኝነትና የዘር ጥላቻ ትርክቶች ለመረዳት በጥልቀት መመርመር ይኖርብናል፡፡ እነዚህ የጥላቻ ድርጊቶች በመድልዖ እና በነጭ የበላይነት ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ እኛ ማናቸውንም ዓይነት የዘር ጥቃት የምናወግዝ ሲሆን ይህን ጥላቻ ለማስቆም የሚያስፈልገው የባሕል ለውጥ እንዲደረግ ለመደገፍ በጽናት ቆመናል፡፡

እንደ ድርጅት በማሕበረሰባችን ውስጥ ያለውን ዘረኝነት ለመታገል ሚናና ሃላፊነት አለብን፡፡ የእኛ ራዕይ ሁሉም ስኬታማ የሚሆንበት ጠንካራ ማሕበረሰብ ነው፡፡ በዘር ርትዕ ጉዳዮችና ፍትሃዊ ባልሆኑ ሥርዓቶች ውስጥ ያለንን ሚና በመመርመር ረገድ ትምህርት ለመውሰድና ለማደግ ቁርጠኛ ነን፡፡ ማሕበረሰባችን፣ ተገልጋዮቻችን እና አጋሮቻችን በ APALA’s Stand with APALA Against Anti-AAPI Racism አማካይነት ለሌሎች እንድታካፍሉ እያበረታታን በዚህ ጉዞ ውስጥ ጉልህ ድርጊት በማድረግ ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ 

ለእስያና የፓሲፊክ ደሴቶች ማህበረሰብ አባሎቻችን የምንገልጸው ከጎናችሁ ለመቆም ቁርጠኞች ስንሆን በእነዚህ ልዩ በሆኑ አስቸጋሪ ጊዜያት በምን መንገድ ልንደግፋችሁ እንደምንችል ማናቸውንም አስተያየት እንድትሰጡን እንጋብዛለን፡፡

ወዳጃችሁ፤

ሚሼል ጄስክ፤ የከተማው የቤተመጻሕፍት ባለሙያ

ሌሎች ማጣቀሻዎች፤

The Asian Pacific Development Center

Live therapist-led group sessions for Asian Communities

Asian Pacific American Librarians’ Association’s 2021 COVID-19 anti-xenophobia 

Anti-racist information resources and COVID-19 Anti-Asian Racism Resources for K-12.