በኮቪድ-19 ዝጋት (COVID-19) - ዘውትር የሚነሱ ጥያቄዎች

የመጽሐፍ መመለሻ አገልግሎት አለ?

ተጨማሪ መረጃ እስከሚገኝ ድረስ ሁሉም የመጽሐፍ መመለሻ አገልግሎቶች ዝግ ናቸው።

ለራሴ መጽሐፎችን አዘዝኩኝ፣ ለመቼ ይደርሱልኛል?

የታዘዙት ዕቃዎች ሁሉ ወረፋ ላይ እንዳሉ ይቆያሉ። ግን ቤተ-መጽሐፍቱ እንደገና እስከሚከፈት ድረስ ምንም አይነት ነገር ልናውሶት እንችልም።

ለኔ የመጡ መጽሐፎች ለመዋስ ዝግጁ ከሆኑስ?

ለእርሶ የታዘዙት መጽሐፎችን ዳግም ቤተ-መፃህፍቱ እስከሚከፈት ድረስ ከመያዛችን በተጨማሪ ቤተ-መፃህፍቱ ከተከፈትም ቦሃላም ለአንድ ተጨማሪ ሳምንት እኒዝሎታለን።

የተዋስኯቸው ዕቃዎች ጊዜያቸው አልፏል። እነሱን እንዴት መመለስ እችላለሁ?

በሁሉም ቅርንጫፎች የሚገኙት የመጽሐፍ መመለሻ አገልግሎቶች ዝግ ናቸው። እባክዎን ቤተ-መፃህፍቱ እንደገና እስኪከፈት ድረስ የተዋሷቸውን ዕቃዎች ይያዙ። የመጨረሻ መመለሻ ቀኖችንን አራዝመናል።

አዲሱ የመመለሻ ቀን ምንድን ነው?

ማንኛውም ያዋስናቸውን ዕቃዎች የመመለሻቸውን ቀን እስከ ሜይ 1 2020 ድረስ አራዝመናል።

ይህ ማለት ቤተ መፃህፍቱ እስከ ግንቦት 1 ድረስ ተዘግቷል ማለት ነው?

እይደለም። የከተማ እና የቤተ-መፃህፍቱ አመራር ዳግም ለመከፈት ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ በሚወስኑበት ጊዜ ቤተ-መፃህፍቱ እንደገና ይከፈታል።

ቤተ-መጽሐፍቱ ዝግ እያል እቃዎችን ለመዋስ መጠየቅ እችላለሁ?

በዴንቨር የህዝብ ቤተ-መፃህፍት፣ በፕሮስፔክተር እና በወርልድካት አማካኝነት ይሚገኘው ለመዋስ የመጠየቂያ አገልግሎቶች ቤተ-መፃህፍቱ በተዘጋበት ወቅት ለጊዜው ዝግ ናቸው።

የቤተ-መጽሐፍቱን አገልግሎቶችን ታዲያ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ቅርንጫፎቻችንና የተለያዩ ዕቃዎቻችንን ለጊዜው ባይገኙም ሌሎች የኦንላይን አግልግሎታች፣ የቤተ-መጽሐፍት ዳታቤዞች፣ ኢሚዲያ እና የአስክ አስ ውይይት አገልግሎቶች ቤተ-መጽሐፍቱ በተዘጋበት ወቅት በድህረገፃችን አማካኝነት ክፍት ናቸው።